Ethiopian Evangelical chruch Mekane Yesus in Stockholm
የብስራት መፅሔት
የትምህርቱ ዓላማ
I. የትንቢት አገልግሎትን እና የነቢይነት ጥሪ በተመለከተ የጋራ መረዳትን በቤተ ክርስቲያን ለመፍጠር
II. የትንቢት አገልግሎትን እና የነቢይነት ጥሪ ለቤተ ክርስቲያን የተሰጠ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያንን እና ምዕመናንን ለማዘጋጀት::
III. ከወቅቱ በትንቢትና በነቢያት ዙሪያ ከሚናፈሰው ወሬ እና ውዥንብር እንዲሁም የጥፋት አቅጣጫ ቤተ ክርስቲያንን እና ምዕመናንን ለመጠበቅ
ትንቢት እና ነቢያት
ሁለተኛ ሳምንት
ነቢይ የነቢይነት ጥሪ አገልግሎቶች
1. የ እግዚአብሔርን መልዕክት ወይም የፍርድ ቃል ለህዝቡ መናገር (የእግዚአብሔር ድምጽ ነው::)
2. ስለ ወደፊት ትንቢት መናገር
3. በመገለጥ ማወቅ (የተሰወረን ማወቅ/መግለጥ) የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ። (ሉቃ 7፥39)
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
የሙዚቃ ሚና
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ
በቄ ብሩክ ዉብሸት
ሙዚቃ ከእግዚአብሄር የተሰጠን ትልቅ ስጦታ ነው። ማርቲን ሉተር በአንድ ወቅት ’”ከስነ መለኮት ቀጥሎ ትልቁን ክብርና ስፍራ የምስጠው ለሙዚቃ ነው’’ ብሏል ።(ቤይንተን፣ 1951፤346) እንዳለውም በሕይወት እስከነበረበት ጊዜ ድረስ ሙዚቃ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ያለው ትልቅ ስፍራ እንዲታወቅና እንዲጠበቅ ጥሯል።
ሙዚቃ የሚለው ቃል መዝሙርንና ዜማን አጠቃሎ ይይዛል። በተናጠል ሲብራሩ መዝሙር ማለት ልዩ ልዩ ስልትና ቃና ባለው ድምጽ የሚዜም ግጥም ነው። ወይም መዝሙር በዜማ እቃ የሚቀርብ መንፈሳዊ ማህሌት ነው ።(በእርግጥ የሙዚቃ መሳሪያ የማይጠቀሙ የሀይማኖት ክፍሎች አሉ፣ ለምሳሌ Quakers የሚባሉ)።
በእግዚአብሄር ቃል የተዘጋጀን እንሁን
በቄ ብሩክ ዉብሸት
በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ። 1 ጴጥ 3፡15
ሰዎች አስቀድመው እንደሚመጣ (እንደሚሆን) ያወቁት ነገር አያስደነግጣቸውም፤አያስገርማቸውምም። ሐዋሪያው ጴጥሮስ በ 1 ጴጥ 3፡15 ላይ አማኞች ስለ እምነታቸውና በእምነታቸው ላይ የሚነሳ ጥያቄ እንደሚመጣ አውቀው ዘወትር ለመልስ ተዘጋጅተው እንዲገኙ መመሪያ ይሰጣቸዋል።
በዚህ ክፍል ላይ የተጠቀሰው ’መልስ’ የሚለው ቃል አፖሎጂ ከሚለው የግሪክ ቃል የተተረጎመ ነው።።አፖሎጂ የሚለው
የግሪክ ቃል መከላከል፣ የያዙት አቋም ትክክል ስለ መሆኑ ማስረጃ እየሰጡ ማብራራት፤ ለጥያቄዎች መልስ መስጠት
ማለት ነው። ጥያቄዎቹ በሁለት አቅጣጫ እንደሚመጡብን አውቀን ሁልግዜ ልንዘጋጅ ያስፈልጋል።
አድራሻ ADDRESS
EECMY in Stockholm C/O Bodholmsplan 1, 127 48, Skärholmen, Sweden
ስልክ Telephone 0762447829 /08-6809439 / 0700443486
የባንክ ቁጥር Bank Acc 106 7544-5 ኢሜይል E-mail info@mekaneyesus.org
Copyright @ All Rights Reserved